Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በትግራይ ክልል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በተያዘው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑ ወጣቶችን ለማሳተፍ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

ከሰኔ 20 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መስከረም አጋማሽ 2017 ዓ.ም ድረስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ የሚሆኑ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች በ14 የልማት መስኮች እንደሚሳተፉ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሀይሽ ሱባጋድስ ገልፀዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የሚሳተፉ ወጣቶች ከሚያገኙት የአዕምሮ እርካታ በተጨማሪ ይወጣ የነበረን ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን የሚያስችል ተግባር ላይ እንደሚሰማሩም ገልፀዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከሚሳተፉ ወጣቶች መካከል 20 ሺህ ያህሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መሆናቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ በአረንጓዴ አሻራ ልማት፣ በጤና፣ በእርሻና ተፈጥሮ ሃብት፣ በትምህርት፣ በደም ልገሳና አረጋውያንን እና አቅመ ደካማ ወገኖችን በማገዝ ላይ እንደሚሳተፉ አቶ ሀይሽ አስረድተዋል።

 

 

Exit mobile version