Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩክሬን ስሎቫኪያን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ዩክሬን ስሎቫኪያን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ስሎቫኪያ 17ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ጎል ስትመራ ቆይታ፤ ዩክሬን በ54ኛው እና በ80ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች።

በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ስሎቫኪያ ቤልጂየምን 1 ለ 0 ያሸነፈች ሲሆን÷ ዩክሬን ደግሞ በሮማንያ 3 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version