የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቤላሩስ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

June 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የቤላሩስ አምባሳደር ፓርቬል ቪዚያትኪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ መደበኛ የፖለቲካ ምክክር በማካሄድ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያና ቤላሩስ በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ግብርና፣ ትምህርት እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡