የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ከቤጂንግ ኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ዋና ጸሃፊና የቤጂንግ የአመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

June 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ዋና ጸሃፊ እና የቤጂንግ የአመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ሊ ዌይ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም ÷ሁለቱ እህትማማች ከተሞች በቀጣይ በትራንስፖርት፣ በቤቶች ግንባታ፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ሁለቱ ከተሞች የነበራቸውን የትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡