የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

June 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ከሆኑት ክላቨር ጋቴትን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ በመጭው ሐምሌ ወር የምታስተናግደው 4ኛዉ ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ በጋራ መሰራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

“አፍሪካ አዳራሽ “የተሰኘው የኮሚሽኑ አዳራሽ የእድሳት ስራ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ከሚገኘው የኮሪደር ልማትና ከተገነቡት የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ጋር በማስተሳሰር አንድ የቱሪስት መስህብ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ሁለቱ የሥራ ኃላፊዎች ኮሚሽኑና ኢትዮጵያ በልማትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተባብረው መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።