Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብሪክስ ሀገራት ዐቃቤ ሕግ ሐላፊዎች ስብሰባ የጋራ ስምምነት መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በብሪክስ አባል ሀገራት የዐቃቤ ሕግ አመራሮች መካከል ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ የጋራ የስምምነት መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል፡፡

ከሰኔ 10 እስከ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የብሪክስ ሀገራት የዐቃቤ ሕግ ሐላፊዎች ፎረም ዲጃታል መፍትሔ ለወንጀል መከላከል እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚል መሪ ሃሳብ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ተሞክሮ እና በፍትህ ዘርፍ ያለውን ዲጃታል መፍትሔ ለወንጀል መከላከል እና የሕግ የበላይነት እየተከናወኑ ያሉ ተሞክሮዎች በፍትህ ሚኒስቴር የዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ዳባ ቀርቧል፡፡

በዲጃታል መፍትሔ ለወንጀል መከላከል እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የብሪክስ አባል ሀገራትን ትብብር እና ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ በስፋት ዉይይት ከተደረገ በኋላም የጋራ የስምምነት መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version