የሀገር ውስጥ ዜና

በወላይታ ዞን ባለፉት 11 ወራት በትራፊክ አደጋ የ53 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Amele Demsew

June 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 11 ወራት በትራፊክ አደጋ የ53 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 77 ወገኖች ደግሞ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የወላይታ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በመንገድ ደኅንነትና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያለመ የእግር ጉዞ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷ በዚሁ ወቅትም ሕብረተሰቡ እራሱን ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከል ግንዛቤ የሚፈጥሩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራትም በትራፊክ አደጋ ምክንያት የ53 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ÷ በ54 ሰዎች ላይ ከባድ እና ከ23 በሚልቁ ወገኖች ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን መምሪያ አስታውቋል፡፡

የትራፊክ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስም÷ ሕብረተሰቡ፣ አሽከርካሪው፣ እግረኛው እና የትራንስፖርት ዘርፍ ባለሙያዎች በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በማስተዋል አሰፋ