አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሰረት ማድረግ ይገባናል”ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ÷የአዘርባጃንን ምርጥ ተሞክሮ በመውሰድ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዛሬ ከሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስትሪንግ ኮሚቴ አባላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡