አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ከታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ኮሚሽን ጋር በመተባበር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ 44 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጉ ተገለጸ፡፡
ፍልሰተኞቹ ከእስር ተፈትተው የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ዛሬ የመጀመሪያ ዙር ተመላሾት ወደ ሀገር ቤት እንዲሸኙ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
በተያያዘ በታንዛኒያ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዜጎችን በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከሚመለከታቸው የሀገሪቱ ተቋማት ጋር እየተሠራ መሆኑን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡