የሀገር ውስጥ ዜና

በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

By Shambel Mihret

June 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል፡፡

ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማ ከሚገባው አጠቃላይ የውሃ መጠን በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል።

በዚህም የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በማቃለል ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡