አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ45 ሚሊየን ብር የተገዙ 110 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረክቧል፡፡
ሞተር ሳይክሎቹ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንደሚውሉ ተገልጿል፡፡
ድጋፉ እየተገነቡ ያሉ የውሃ ተቋማትን ክትትል ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ለ55 ወረዳዎች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሞተር ሳይክሎች መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ክልሎች ሞተሮችን ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲያውሉ መገለጹንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡