Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፖሊስ ጀልባዎችን ለማሰራት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የፖሊስ ጀልባዎችን ለማሰራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የሚሰሩ ጀልባዎች ዲዛይናቸው እና የጥራት ደረጃቸው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በጣልያንና በቻይና ሀገራት እንዲሁም በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገመገመና አዎንታዊ ምላሽ ያገኘ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ጀልባዎቹ ሀገር በቀል በሆነው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሀገር ውስጥ መሰራታቸው በኢትዮጵያ የተጀመረውን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚያፋጥን ተጠቁማል፡፡

ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሥራ አገልግሎትን የበለጠ የሚያዘምን እና ተደራሽነቱን የሚያሳድግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥበቃ እና ሌሎች ውሃማ አካላት ያሏቸውን ተቋማት ደህንነት ለመጠበቅ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ጀልባዎቹ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ያለው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር የራሳቸው አበርክቶ እንደሚኖራቸውም ተነግሯል፡፡

Exit mobile version