Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ አረጋ ከበደ በባሕር ዳር የልማት ሥራዎች እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በጉብኝታቸው የልማት ሥራዎችን የአፈጻጸም ደረጃ እየተመለከቱ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ከምልከታው በኋላም የቀጣይ አቅጣጫ እና መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

Exit mobile version