አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል ሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ወታደሮች እያስመረቀ ነው።
ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዛሬ በመሠረታዊ ወታደርነት እያስመረቃቸው የሚገኙት ወታደሮች የ8ኛ ዙር ሰልጣኞች መሆናቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተመራቂዎቹ በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው የቀሰሙትን የንድፍና የተግባር ወታደራዊ ስልጠና በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ በኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር በመከላከያ ህብረት የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንንኖች እንዲሁም አባገዳዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።