Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች የህዝቡን ጥያቄ እየፈቱ የሚገኙ ናቸው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች የህዝቡን ጥያቄ እየፈቱ የሚገኙ ናቸው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የመሰረተ ልማት ስራዎች የግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ÷ የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

በመሰረተ ልማት ግንባታ ረገድ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ እየፈቱ የሚገኙ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በመሰረተ ልማት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ በመንገድ ልማት ስራዎች የሕብረተሰብ ተሳትፎ የንቅናቄ ሠነድ ዙሪያ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሏል፡፡

በመድረኩ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

Exit mobile version