የሀገር ውስጥ ዜና

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

By Meseret Awoke

June 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ መሆኑን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፓስፖርት ማደስ፣ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣ የተበላሸ ወይም እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።