የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሚኒስትሯ ከጣሊያን አምባሳደር ጋር መከሩ

By Feven Bishaw

June 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) ከኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎሰቲኒ ፓሌዝ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ ታሪካዊ የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ትብብሮችን ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አምባሳደር አጎሰቲኒ በውይይቱ ወቅት ÷ከኢትዮጵያ ጋር በሁለንተናዊ መልኩ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሠራዊት ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡