የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የ6ኛ ክፍል ፈተና ይሰጣል

By Shambel Mihret

June 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው እንዳስታወቀው÷ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86 ሺህ 222 ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል፡፡

በፈተና ጣቢያዎቹም ከ2 ሺህ 200 በላይ ፈታኞች፣ ከ700 በላይ ሱፐር ቫይዘሮች፣ 183 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ፈተናውን ለማስፈጸም መመደባቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡