አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “የተደራጀ የሲቪል ማህበራት ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልጽግና “ በሚል መሪ ቃል በከተማችን ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።
የሲቪል ማኅበራት የተለያዩ የማህበረሰብ አካላትን የሚወክሉ፣ በዴሞክራሲ ማበብ፣ መጎልበት እና ማኅበራዊ ፍትህ በማንገስ ረገድ የላቀ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
“በመሆኑም በከተማችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት እንዲሁም የተሻለ የግንኙነት አግባብን በመከተል ተቀራርበን በጋራ ለመስራት በውይይታችን ወቅት ተስማምተናል” ነው ያሉት።