አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለ2016/17 የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው 700 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከ400 ሺህ ኩንታል በላይ ለአርሶ አደሮች መድረሱ ተገለጸ፡፡
ቀሪው 300 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ ኢያሱ አብረሃ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡
እንዲሁም ለምርት ዘመኑ ከሚያስፈልገው 150 ሺህ ኩንታል የጤፍና የስንዴ ምርጥ ዘር 40 ሺህ ኩንታል መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡
በአንዳንድ የክልሉ ዞኖች ዝናብ መጣሉን ተከትሎም ማሽላ፣ በቆሎ እና ዳጉሳ መዘራቱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥሉት ወራት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚኖረውን ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ ሊኖር ስለሚችል ከወዲሁ አርሶ የጎርፍ መከላከያ በመሥራት እርጥበትን የሚቋጥሩ ሥራዎችን እንዲያከናወን አሳስበዋል፡፡