አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተገኝተዋል፡
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡