አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክልሉ በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኘው የእምነቱ ተከታቶች ከማለዳው ጀምሮ ሐረር በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታድየም በመሰባሰብ በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።
በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ም/ቤት አፈጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሃይማኖት አባቶችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡