አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባዋ በመልእክታቸው÷”እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ዓ.ሂ ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ አል አድሃ” ብለዋል፡፡
ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስተላልፈዋል፡፡
በተመሳሳይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባው በመልዕክታቸው፥ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የአረፋ በዓል ሰዎችን በፍቅር እርስ በእርስ የሚያስተሳስር በርካታ እሴቶችን የያዘ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህሉን በማጠናከር የአስተዳደሩን ሰላም፣ አብሮነት፣ አንድነት በማጠናከር ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡