Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚ ገንብታለች -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እድገቷ ያልተቋረጠ፣ በብዙ ፈተናዎች ውስጥም ቢሆን እንኳን እድገቷ ያልተገታ፣ ጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ የማክሮ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቻለች ሀገር መሆኗ የተመሰከረበት ነበር ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳች ላይ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የ7 ነጥብ 9 ምጣኔ ሃብታዊ እድገት በፈጣን እድረት ውስጥ ያለች ሀጋር መሆኗን ያሳያል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 10 ወራት ኢትዮጵያ እድገቷ ያልተቋረጠ፣ በብዙ ፈተናዎች ውስጥም ቢሆን እንኳን እድገቷ ያልተገታ፣ ጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቻለች ሀገር መሆኗ የተመሰከረበት ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚና ዋና ዋና ዘርፎች አፈፃፀምን በተመለከተ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል ያሉት ሰላማዊት ካሳ ÷ለማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ ተልቅ አስተፅኦ ካደረጉት መካከል የግብርናውን ዘርፍ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም በመኸር ወቅት በዋና ዋና ሰብሎች ለማምረት ታቅዶ የነበረው 513 ሚሊየን ኩንታል መሆኑን ተናግረው ÷ባለፉት 10 ወራት በመኸር ወቅት 506 ሚሊየን ኩንታል ለማግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

ይህም የአጠቃላይ እቅዱን ወደ 98 በመቶ ማሳካት የሚያስችል ሲሆንካምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀ ርም አምና በመኸር ወቅት 393 ሚሊየን ኩንታል መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ሆርቲካልቸርም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ ነበር ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ÷አምና ከዘርፉ 122 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸው ዘንድሮ ወደ 340 ሚሊየን ኩንታል ከፍ ብሏል ብለዋል፡፡

የመስኖ ስንዴ ልማት በተመለከተ አምና 47 ሚሊየን ኩንታል መገኘቱን ተናግረው÷ ዘንድሮ 106 ሚሊየን ኩንታል ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ይህም በሀገራዊ አንድምታው ምርትና ምርታማነት ላይ በስፋት መሰራቱና ያሉንን ተፈጥሯዊ ሃብቶች መጠቀም ላይ ማተኮራችን ውጤት እያስመዘገባ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

የሩዝ ምርትን ስንመለከት አምና 9 ሚሊየን ኩንታል የለማ ሲሆን÷ ዘንድሮ 37 ሚሊየን ኩንታል የሩዝ ምርት ማግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ባለፉት 10 ወራት አምራች ኢንዱስትሪው በሀገር ውስጥ ያለው የገበያ ድርሻ 40 በመቶ ለማድረስ ነበር የታቀደው ፤ በዚህም 39 በመቶ የገበያ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፤በዚህም የኤሌክትሪክ ገመድን ጨምሮ ተያያዥ ቁሶችን በሀገር ወስጥ ማምረት ተችሏል፤17 ሚሊየን ዶላር ማስቀረት ተችሏልም ብለዋል፡፡

እንዲሁም ትራንስፎርመርን በሀገር ውስጥ በማምረት 47 ሚሊየን ዶላር ፤የድንጋይ ከሰልን እንዲሁ 65 በመቶ የሚሆነውን ፍላጎት በሀገር ውስጥ አምርቶ መሸፈን ተችሏል ነው ያሉት፡፡

እንዲሁም የብቅል ምርትን በሀገር ውስጥ በማምረት 228 ሚሊየን ዶላር ወጪን ፤ፓስታ ፣ማካሮኒ ፣የሕፃናት አልሚ ምግቦችን ጨምሮ ሌሎችን የፍጆታ እቃዎች በሀገር ውስጥ በማምረት ደግሞ በ 458 ሚሊየነር ዶላር ማስቀረት ተችሏል፡፡

በተጨማሪም የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ በማምረት 200 ሚሊየን ዶላር ማስቀረት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

Exit mobile version