የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 787 ተማሪዎች አስመረቀ

By Amele Demsew

June 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በአውሮፕላን አብራሪነት፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በንግድና በአውሮፕላን ጥገና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 787 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ኃላፊ ረታ መላኩ÷የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ታድመዋል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ብቃት ያላቸውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ረገድ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል ።

በዚህም የሰለጠነ ሙያተኛን በማፍራትና በማብቃት ወደ ስራ እንዲቀላቀሉ እያደረገ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያን አየር መንገድ ግሩፕ በየጊዜው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን እያሰፋ የአውሮፕላን ቁጥር እየጨመረና ብቁ የሰው ሃይል እያፈራ በአፍሪካ የአቪዬሽን መስክ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም አስታውሰዋል።