Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ተኛው አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

ኮንፍረንሱ”የጋራ ሀብት ለጋራ መጻኢ ጊዜና ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት፤በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ጨምሮ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ወሌ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣የናይል ተፋሰስ ሀገራት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

መድረኩ በናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለሚኖር ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Exit mobile version