Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነባ የሚገኘውን የአርሶ አደሮች የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነባ የሚገኘውን የአርሶ አደሮች የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷በክልሉ እየተገነባ የሚገኘው የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ህገ ወጥ ንግድን ለማስቀረትና አምራቹ እና ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበያይ ያግዛል፡፡

በክልሉ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

የማዕከሉን ግንባታ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።

በ3ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈው ማዕከሉ 250 የንግድ ቤቶችን ጨምሮ ሁለት አነስተኛ አዳራሾችና ካፌን የያዘው መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version