Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

36 በመቶው የመድሃኒትና የህክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ አሁን ላይ 36 በመቶውን የመድሃኒትና የህክምና ግብአት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ።

የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅዳስ ዳባ በግምገማ መድረኩ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት÷በእናቶች፣ በህፃናትና ጨቅላ ህፃናት ህክምና አገልግሎት ዙሪያ የነበሩ ችግሮችን በማቃለል የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመድሃኒትና ሌሎች የህክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ መቻሉንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የመድሃኒትና የህክምና ግብአቶች የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ 8 በመቶ እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ 36 በመቶ የሚሆነውን የመድሃኒትና የህክምና ግብአት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን ተችሏል ብለዋል።

የሀገር ወስጥ አምራቾች እንዲበረታቱና አዳዲስ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ መደረጉ ለስኬቱ ቁልፍ ክንውኖች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም ባለፉት 100 ቀናት ብቻ ሁለት አዳዲስ የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ሀገር ውስጥ ገብተው ማምረት ጀምረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመድሃኒት ልማትና አቅርቦት ከሀገር ውስጥ ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ ለአህጉራዊ ተደራሽነት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version