Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጤና ዘርፍ የሚካሄዱ ምርምሮች የዘርፉን ፖሊሲ ለማጠናከር ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ እየተካሄዱ ያሉት ጥናትና ምርምሮች የዘርፉን ፖሊሲ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጤና ሚኒስቴር አስገነዘበ፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት ሀገራዊ የጤና ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

በሚኒስቴሩ የፖሊሲ ጥናት፣ ልማትና ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እንደገና አበበ በጉባዔው ላይ እንዳሉት÷ በጤና ዘርፍ በተመራማሪዎች እየተካሄዱ ያሉ ጥናትና ምርምሮች ለጤና ፖሊሲዎች መሰረት ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ችግሮችን የሚቋቋምና ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት እየተሠሩ ባሉት ሥራዎች የምርምሮቹ ውጤቶች ላቅ ያለ ድርሻ እየተጫወቱ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ጥናትና ምርምሮቹ ለጤናው ዘርፍ ፖሊሲ መሰረት እንዲሆኑ ጥራታቸውን ጠብቀው የተሠሩ ምርምሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ታፈሰ ማቲዮስ (ዶ/ር) በበኩላቸው በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ በተለያዩ መስኮች ላይ ያተኮሩ 163 ምርምሮችን ተቋማቸው እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በቢቂላ ቱፋና ታመነ አረጋ

Exit mobile version