Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ክለብ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ኢንተር ማያሚ ክለብ ማጠናቀቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡

የ8 ጊዜ ባለንዶር አሸናፊው ሜሲ የፈረንሳዩን ክለብ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን በመልቀቅ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ አሜሪካ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡

“ኢንተር ማያሚ የመጨረሻው ክለቤ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” ሲል የ36 ዓመቱ ሜሲ ለኢ.ኤስ.ፒ.ኤን ተናግሯል፡፡

“ከእግር ኳስ ለመገለል ግን ዝግጁ አይደለሁም” ሲልም አክሏል፡፡

ሜሲ በዚህ ዓመት ለክለቡ ባደረጋቸው 12 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ፥ 13 ለግብ የሚሆነ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር በፈረንጆቹ 2022 የዓለም ዋንጫን ያነሳው ሚሲ ፥ በኢንተር ማያሚ ክለብ እስከ 2025 ድረስ የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን ፤ ውሉን ለተጨማሪ ጊዜ የማረዘም እድልም አለው፡፡

ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና ቆይታው 10 የላሊጋ ድሎችን ጨምሮ 4 ጊዜ የሻምፒንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version