Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህር ዳር ከተማና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የባህር ዳር ከተማን ግቦች ፀጋዬ አበራና ያብስራ ተስፋዬ አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግቦች ደግሞ አዲስ ግደይ (ፍ) እና ቢኒያም ጌታቸው ከመረብ አሳርፈዋል።

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

Exit mobile version