አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ የ43 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱል ካማራ ተፈራርመዋል፡፡
ድጋፉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር እንደሚውል የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡