Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት የተላከ መልዕክት ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ የተላከ መልዕክት ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀበሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ዛሬ ጠዋት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ መልዕክት ከፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ ይዘው መጥተዋል” ብለዋል።

እንዲህ ያሉት ግንኙነቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ለንግግር እና ትብብር አውታር በመሆን የጋራ መግባባትን ያሳድጋሉ ሲሉም ገልጸዋል።

Exit mobile version