Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“በምክክር ትዳን ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “በምክክር ትዳን ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፅናት ለኢትዮጵያና ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበራት በጋራ “በምክክር ትዳን ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በምክክሩ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ በማስተላለፍ ግንዛቤ የመፍጠሪያ ዘመቻ ሲያካሂዱ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ማህበራቱ ዛሬ እንደ ሀገር ለብዙ አመታት ይዘናቸው የተጓዝናቸው አጨቃጫቂ ሀገራዊ ትርክቶቻችን በሀገራዊ ምክክሩ ምን አይነት መፍትሔ ሊበጅላቸው ይችላል በሚልና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ የፓናል ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)÷ ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራት እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡

በመድረኩ የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ተሳታፊዎች እየተወያዩባቸው እንደሚገኙም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version