አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቢሲንያ ባንክ ለ2ኛ ጊዜ ያዘጋጀው “አሚን አዋርድ” የሥራ ፈጠራ ውድድር ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ባንኩ አስታውቋል፡፡
“አሚን አዋርድ” የሥራ ፈጠራ ውድድር ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳቦችን በከፍተኛ ፉክክር ሲያሳትፍ መቆየቱ ተመላክቷል፡፡
አሁን ላይም በውድድሩ ሲሳተፉ ከነበሩ 180 ተወዳዳሪዎች መካከል 126ቱ መመረጣቸው ነው የተገለጸው፡፡
ተወዳዳሪዎቹ በቴክኖሎጂ ግብዓቶች፣ በግብርና ምርቶች፣ በግንባታ ቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በንግድ ፣ በታዳሽ ሃይል፣ በትምህርት፣ በጤና እና በኢ-ኮሜርስ ዘርፍ ሃሳባቸውን ለውድድር አቅርበዋል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ በማግኘት አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች÷ ባንኩ ከ200 ሺህ ብር እስከ አንድ ሚሊየን ብር የፕሮጀክት ሃሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ የሥራ ማስኬጃ ሽልማት ይስጣል ተብሏል።
በዕለቱም በተለያዩ በጎ ሥራዎች ተሰማርተው ማህበረሰቡን ለሚያግዙ 6 ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ባንኩ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡
በሲሳይ ጌትነት እና ሃይለማሪያም ተገኝ