አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ክልላዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎትን በባሕር ዳር ከተማ አስጀምረዋል።
በመርሐ ግብሩ ከአቶ አረጋ በተጨማሪ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራው በክልሉ በሁሉም ከተሞች እንደሚተገበር ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አቶ አረጋ ÷ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በበጎ ፋቃድ አገልግሎት ሥራው ላይ እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።