አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተከታይ ያለውን ቲክቶከር ጨምሮ ያልተጠበቁ ግለሰቦች የአውሮፓ ፓርላማ መቀመጫን ማሸነፋቸው ተሰምቷል፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ በአውሮፓውያን ብቻ ሣይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠበቁት ምርጫዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩና የዓለምን ፖለቲካ በመረዳት ለሀገራቱም ይሁን ለህብረቱ አባል ሀገራት ይወክላል የተባለ ፖለቲከኛ መቀመጫውን ለማሸነፍ ምርጫ ይካሄዳል፡፡
በምርጫውም ያሸነፈ ግለሰብ ለወከለው ህዝብ ጥቅም መከበር ጥረት የሚያደርግ ሲሆን፥ እንደሚታወቀው ግለሰቡ በብዙ የፖለቲካ እውቀትና በዘርፉ የላቀ መረዳት ውስጥ ሊያልፍ ግድ ይለዋል፡፡
ሆኖም አሁን ላይ በተለያዩ የአውሮፓ ፓርላማን መቀመጫ በማሸነፍ ለመሪነት የተቀመጡ አንዳንድ እጩዎች እንደሚታሰበው ፖለቲከኛና በዘርፉ ልምድ የቀሰሙ እንዳልሆኑ የዘገበው አሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡
ከእነዚህ መካከል ደግሞ ቆፕሮሳዊው ፊዲያስ ፓናዮቱ አንዱ ሲሆን፥ የፖለቲካ ዕውቀትና ልምድና እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት የሌለው የ24 ዓመቱ ወጣት ቲክቶከርና ዩትዩበር ነው፡፡
ወጣቱ በዩትዩብ ያገኛቸውን 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተከታዮቹ የአውሮፓ ፓርላማ መቀመጫን አሸናፊ እንዲሆን አድርገውታል ተብሏል፡፡
ይህ ግለሰብ የፖለቲካ ተሳትፎም ሆነ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ግንኙነት የለውም መባሉ ዓለምን እያነጋገረ ነው፡፡