አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት ማንጋፍ ግዛት በመኖሪያ ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ የ41 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
አደጋው የቤት ውስጥ ሰራተኛ የሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች በብዛት በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ መከሰቱ ነው የተገለጸው፡፡
በእሳት አደጋው ቢያንስ የ41 ሰዎቸ ሕይወት ማለፉንና በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የኩዌት ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በአደጋው ለህልፈት የተዳረጉት የውጭ ዜጎች ማንነት አለመለየቱን የጠቆመው ሚኒስቴሩ÷ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሕንጻው ባለቤት መታሰሩን ገልጿል ፡፡
አሁን ላይ የእሳት አደጋው በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን÷ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አልጄዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡