የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ከ58 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ ኮምፖስት አዘጋጀሁ አለ

By ዮሐንስ ደርበው

June 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም በመደበኛ ኮምፖስት ዝግጅት ከ58 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ መዘጋጀቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከተዘጋጀው አጠቃላይ ኮምፖስትም 42 ሚሊየን 997 ሜትር ኪዩቡ ከአፈር ጋር ተዋኅድ ጥቅም ላይ መዋሉን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡

በኮምፖስት ዝግጅቱ ከ2 ሚሊየን 190 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

በ2016/17 የምርት ዘመን 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን እና ዕቅዱን ለማሳካትም የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡