Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች መሰራጨታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የዘንድሮው የንብ እርባታና የማር ሀብት ልማት የዕቅድ ክንውን ግምገማና የዘርፉ የ2017 በጀት ዓመት ላይ ያተኮረ መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ቶሌራ ደበላ እንደገለፁት÷ ክልሉን የማር ልማት ማዕከል ለማድረግ ኢኒሺዬቲቭ ተቀርጾ ወደ ተግባር ተገብቷል።

እስከ በጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ድረስ 1 ሚሊየን ዘመናዊ ቀፎዎችን ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት እየሰሩ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

እስከ አሁንም ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ ቀፎዎች ተደራሽ መደረጋቸውን በመግለጽ ንብ ወደ ቀፎዎቹ የማስገባት ተግባር በባህላዊና በሳይንሳዊ መንገድ ተከናውኖ ከ97 ሺህ 300 በላይ ቶን ማር መመረቱን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version