Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች 24 የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም ኤሌክትሪክ አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ስር በሚገኙ 24 የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በአካባቢዎቹ በጸጥታ ችግር ምክንያት የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ተጠግነው ነው ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም አገልግሎት መስጠት የጀመረው፡፡

በምዕራብ ሸዋ በችግሩ ሳቢያ አገልግሎቱ ተቋርጦባቸው የነበሩ 18 ከተሞችና ቀበሌዎች ኤሌክትሪክ ዳግም ማግኘታቸውን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከነዚህም መካከል ቢሎ፣ ቦጂ፣ ጩሉቴ፣ ቲኦ፣ ዶዶታ ፣ ኖኖ ቤንጃና ዲራሙ ተብለው የሚጠሩ አካባቢዎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ደግሞ ጅጅጋ፣ ጎራ፣ ሀደድ እና ተጀብ ተብለው የሚጠሩ ቦታዎችን ጨምሮ 8 ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

Exit mobile version