የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

June 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር አና ፋሩ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ ÷ ኢትዮጵያና ግሪክ በህዝብ ለህዝብ፣ በኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ለዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል መደበኛ የፖለቲካ ምክክር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ ግንኙነት ውስጥ መሻሻል ስላለባቸው ጉዳዮችና ስለ ሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡