የሀገር ውስጥ ዜና

በስልጢ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Amele Demsew

June 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አሳኖ ቀበሌ በነነ አካባቢበደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ዋና ሳጂን አብድረማን ረዲ ገለጹ፡፡

ትናንት ምሽቱ 3 ሰዓት ከ20 ደቂቃ አካባቢ ከወራቤ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ከቡታጅራ ወደ መናኸሪያ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭተው አደጋው መከሰቱን አስረድተዋል፡፡

በአደጋው የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው÷ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑም አመላክተዋል፡፡

በኤርሚያስ ቦጋለ