የሀገር ውስጥ ዜና

የሚኒስትሮች ም/ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ተጀመረ

By Feven Bishaw

June 11, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የሆነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ እንደሁልጊዜው ሁሉ የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በግምገማውም “ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይም ለቀጣይ ሥራዎች እንነሳለን” ሲሉም አመላክተዋል፡፡