አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ 9 ሰዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን መሰወሩ ተነገረ።
የማላዊ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ ንብረትነቱ የሀገሪቱ መከላከያ ሃይል የሆነ አውሮፕላን የማላዊ መዲና የሆነችውን ሊሎንግዌን እንደለቀቀ ከራዳር ውጭ ሆኗል።
የአቪየሽን ባለስልጣናት ከራዳር ውጭ ከሆነችው አውሮፕላን ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ የአውሮፕላኗ ፍለጋ እንዲከናወንና የነፍስ አድን ተግባር ለማከናወን ዝግጅት እንዲደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።