Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መንግስት ፈተናዎችን በብቃት ለማለፍና የሀገሪቱን ገጽታዎች ለመለወጥ እየሰራ ነው – አቶ አሻድሊ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆሳዕና ከተማ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ክብር” በሚል መሪ ሃሳብ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋና በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

አቶ አሻድሊ በወቅቱ እንዳሉት÷የለውጡ መንግስት የሀገሪቱን ገጽታዎች ለመለወጥና ፈተናዎችን በብቃት ለማለፍ እየሰራ ነው፡፡

በተለይ እንደ ሀገር የቆዩ እዳዎችና ስብራቶችን ለመጠገን የለውጡ መንግስት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡

ባለፉት ዓመታት በምግብ ራስን ለመቻል የተደርጉ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ፣ የሌማት ትሩፋትና የተረጂነት አስተሳሰብን ለማስቀረት የተደረጉ ጥረቶች ብሩህ ተስፋ መፍጠራቸውን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓሏዊነትና ክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በሀዋሳ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የሐረሪ ክልል ም/ቤት ም/አፈ ጉብዔ አቶ ሐሪፍ መሃመድ፣ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማሪያም እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Exit mobile version