የሀገር ውስጥ ዜና

በአሶሳና ወልቂጤ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

June 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ክብር” በሚል መሪ ሀሳብ በአሶሳና ወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ የየህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎች በመድረኩ እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ ጸጋዬ ማሞ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።