Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎችን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን የሀገርውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ 6 እጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ በዚህ ወር በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የስድስት እጩዎችን የመጨረሻ ዝርዝር ነው ይፋ ማድረጉ የተሰማው፡፡

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በቅርቡ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ በሄሊኮፍተር አደጋ ህይዎታቸው ማለፉን ተከትሎ ለሀገሪቱ አዲስ ፕሬዚዳንት መምረጥ በማስፈለጉ ነው የሚካሄደው፡፡

ለፕሬዚዳንትነት ከሚወዳደሩት እጩዎች መካከል በሀገሪቱ በምክትልፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙትን አሚርሆሴይን ቃዚዛዴህ ሃሺሚን ን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች እያገለገሉ ያሉ ሃላፊዎች እንደሚገኙበት የአርቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version