Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ ለሚገነባ ሕንጻ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር ሆነው በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ ለሚገነባ ሕንጻ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ገለጹ፡፡

ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር÷ በማፍረስም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ሕንጻዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ ምላሽ ማመስገናቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version