ቢዝነስ

አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

June 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ከተማ አቋርጦት የነበረውን በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል፡፡

ላለፉት ስድስት ወራት ሲካወኑ የነበሩ የጥገና ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው አውሮፕላን ማረፊያ በዛሬው ዕለት ዳግም ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡

በዳግም በረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም÷የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የትግራይ ክልል ጊዜያው አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል፡፡